11 October 2026
"የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
About
ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcast
#sbsaudiopodcast