
10 February 2026
"የኮንፈረሳችን ዓላማ የኦሮሞ ማኅበረሰብን ማገናኘት፣ ስላለፈው መወያየት፣ ለወደፊት ማቀድና መረጃን መለዋወጥ ነው" ኦቦ ተስፋዬ ድፋ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
About
በቪክቶሪያ የኦሮሞ አረጋውያን ደኅንነት እና በጎ አድራጎት ማኅበር ከአውስትራሊያ የኦሮሞ ሲቪክ ድርጅቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የድርጅቶቹ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተፅዕኖ አሳዳሪዎችና የማኅበረሰብ አባላትን ያካተተ፤ በእራት የታጀበ ዓመታዊ ኮንፈረንስ አካሂዷል። ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 14 / የካቲት 7 የማናቸውም ማኅበረሰብ አባላት በፍላሚንግተን የማኅበረሰብ አዳራሽ በመገኘት የአውስትራሊያ መንግሥት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ ባለሙያዎች የሚሰጡን ገለጣዎች በማድመጥ ግንዛቤ እንዲጨብጡም ጋብዘዋል።