የአባቶች ቀን አከባበር በሀገረ አውስትራሊያ
08 September 2025

የአባቶች ቀን አከባበር በሀገረ አውስትራሊያ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

About
አቶ ጉግሳ አሊጋዝ "ለኢትዮጵያውያን ሁሌም የአባቶች ቀን ነው። እኛ ጥሩ አባቶች ነን። ልጆቼን እጅግ በጣም ነው የምወዳቸው፤ በእዚህ ምድር ላይ በጣም ያስደሰተኝ ነገር ቢኖር ከልጆቼ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ነው " ሲሉ፤ አቶ ኃይለማርያም ኃይለየሱስ በበኩላቸው "እግዚአብሔር በልጆች ባርኮኛል፤ ልጆቼን በፍቅር ነው ያሳደግኳቸው። የወላጅ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ ብዬ አስባለሁ። ልጆቼም ለእኔ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት አላቸው፤ የአባቶችን ቀን በጣም ደስ ብሎኝ ነው ያከበርኩት" ይላሉ።