
09 December 2025
"ሼክስፒር እኔ ኮርዴሊያን ሆኜ ስጫወት ቢያየኝ፤ እርግጠኛ ነኝ፤ ጥቁር ሴት በመሆኔ ይደነግጣል። በእሱ ጊዜ ዘረኛነት በጣም ነበር።" ተዋናይት አሁንም አበበ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
About
ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ሲድኒ በትወና ላይ ያለውና ጃኑዋሪ 4 የሚያከትመው የሼክስፒር King Lear ተውኔት ኮርዴሊያን ብቻ አይደለችም። ከተውኔት ባሻገር ስላላት የማኅበራዊ ፍትሕና የተፈጥሮ ክብካቤ አንቂነት ሕይወቷ፣ የሼክስፒር ተውኔቶች ዘመን ተሻጋሪነትና አሁንም ድረስ ገነን ሆኖ የቆየበትን አስባብ አንስታ አተያይዋን ታጋራለች።