Skip to content
Opens in a new window
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ
10 October 2026

ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

About
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል።

#sbsaudiopodcast