
20 January 2026
"ግጥምን በጃዝ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ዒላማ 'ለሰዎች የመዝናኛ መድረክ መክፈት፤ ባሕልን፣ የሀገር ፍቅርንና ዕሴትን ማስተዋወቅ ነው" ተዋናይ ጌታሁን ሰለሞን
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
About
መታሰቢያነቱ ለሰዓሊ ታምራት ገብረማሪያም የተቸረውና ለሁለተኛ ጊዜ የተከወነው 'ግጥምን በጃዝ' የአንድ ሰው ተውኔትን አጣምሮ በዕለተ እሑድ ጃኑዋሪ 18 / ጥር 10 ለሕዝብ ቀርቧል። የመድረክ መሪዎች፣ ገጣሚዎችና የሙዚቃ መሳሪያ ባለሙያዎች አተያያቸውን አጋርተዋል። ለቀጣዩ ዝግጅት ኢትዮጵያውያን በነቂስ እንታደሙ የግብዣ ጥሪያቸውን በጥበብ አንደበት አቅርበዋል።