zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Toggle Sidebar
zeno
SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Daily News
Society & Culture
Amharic
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Website
Episodes
300
30 March 2026
ኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀችው የሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ፎረም ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር የ13 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኅን ባለስልጣን በአንድ ዓመት ውስጥ ከማኅበራዊ ሚዲያዎች በናሙና ከታዩ 32 ሺህ ይዘቶች መካከል ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃዎች መሆናቸውን በጥናት መለየቱን አመለከተ
12 min
29 March 2026
"የፊልም ኢንዱስትሪያችን ገና ዳዴ ማለት እንኳ አልጀመረም" ሶፎንያስ ታድሰ
በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ የዕድገት ደረጃና የአሠራር ሂደቶች ነቅሶ ያመላክታል።
25 min
29 March 2026
"በሚስጥር ከማኅበረሰቡ ውስጥ ተነቅለው የወጡ እውነቶችን የያዘ ነው፤ በሚስጥር ያደረግነው ነገር በአደባባይ ያስለቅሰናል ነው ፅንሰ ሃሳቡ" ሶፎኒያስ ታደሰ
በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ በቅርቡ በአቦል ቴሌቪዥን ለታዳሚዎች ዓይነ ገብ ለመሆን የዕይታ መሰናዶው ስለተጠናቀቀለት ባለ 260 ክፍል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጭብጥ ቀንጭቦ ያጋራል።
19 min
26 March 2026
"ልጄ 'ማሚ እኔ ይኼን ቆዳዬን አልወደምው፤ ቀዪሪልኝ' ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በቃል ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም ነው የከፋኝ።" ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ፤ በሀገር ቤት ጎሠኝነትን፣ በሀገረ አውስትራሊያ ዘረኝነትን እምቢኝ ያሉ፤ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእጅጉ የኩራት ሞገስን የተላበሱ ናቸው። ልጃቸው ዕድሜው አምስት ዓመት ሊሞላ ደርሶ ሳለ የገጠመው የቀለም ልዩነት ያሳደረባቸውን ሥነ ልቦናዊ ሁከት እንደምን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈውስ ሆኗቸው ከእነ ልጃቸው እንደተቋቋሙት ይናገራሉ። ያም አስባብ ሆኗቸው "አድዋና ሜልበርን" ያሏትን የስንኝ ቋጠሮ ያስደምጣሉ።
23 min
26 March 2026
"ጠብን፣ መቀየምን ትፈራለች፤ ፍቅርን፣ ሰው ማክበርን ትወዳለች። በእምነቷም፣ በልጆቿም በትዳሯም ጠንካራ ነበረች።" የወ/ሮ ወርቅነሽ ባለቤት አቶ አብርሃም ተዘራ ገሠሠ
ወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) ለሶስት ዓመታት ከማኅፀን ካንሰር ጋር ያካሔዱት ፍልሚያ አክትሞ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተለይተዋል። ባለቤታቸው አቶ አብርሃም ተዘራ፣ የቤተሰባቸው ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ እና የንስሃ አባታቸው መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ችሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል አስተዳዳሪ፤ የወ/ሮ ወርቅነሽን የሕይወት ዘመን አንስተው፤ ጥልቅ ሐዘናቸውን በመግለፅ ይዘክራሉ። የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ማርች 28 ቀን 2026 / መጋቢት 19 ቀን 2018 በወረቢ ቤተ መቃብር Corner Cemetery Rd & Railway Avenue...
17 min
25 March 2026
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ‘በጣም ትልቅ ስጦታ ሰጠችኝ‘ አሉ
የግሪንስ ፓርቲ አውስትራሊያ ያለ ፓርላማ ይሁንታ ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚደነግግ ሕግ እንዲኖራት ፓርቲያቸው ዳግም መጠየቁን አስታወቁ
6 min
25 March 2026
ኢትዮጵያ በዓለም 5ኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ተባለች
በኢትዮጵያ የዩናይድ ስቴትስ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን የንግድና ጉብኝት ቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የሚደርስ የማስያዣ ገንዘብ እንዲያሲይዙ የሚጠይቀው አሠራር ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ጀምሮ ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ
8 min
24 March 2026
"ኳታር ውስጥ፤ በኑሮ ውድነት ላይ አንዳችም ጭማሪ የለብንም። የነዳጅ ጭማሪ አልተደረገም። መንግሥት ትልቅ ድጋፍ እያደረገልን ነው" ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ
የዶሃ - ኳታር ነዋሪ ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ፤ የእሥራኤል - ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ጦርነት በእሳቸውና በቤተሰባቸው፣ እንዲሁም፤ በኳታር ነዋሪ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደረውና እያሳደረ ስላለው ተፅዕኖ አንስተው ያስረዳሉ።
16 min
24 March 2026
"የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትንና ኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከልን እንደግፍ" ኧኒ ዴቪ እና ማርታ ቦረና
ኧን ዴቪ የFlying Fruit Fly Circus አርቲስቲክ ዳይሬክተርና ማርታ ቦረና የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትና የኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከል ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ቅዳሜ ማርች 28 / መጋቢት 19 ስለሚካሔደው የድጋፍ እራት ፕሮግራምና የእገዛ ፋይዳዎች ይናገራሉ።
16 min
23 March 2026
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰላጤን የባሕር መስመር እንድትከፍት የ48 ሰዓታት ዛቻ አዘል የጊዜ ገደብ ሰጡ
አውስትራሊያ ለአንድ ወር ያህል የሚበቃ የነዳጅ፣ ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ ክምችት እንዳላት አስታወቀች።
6 min