zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Toggle Sidebar
zeno
DW
እንወያይ | Deutsche Welle
Politics
Amharic
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Website
Episodes
50
01 March 2026
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት ልጃለም፤ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ዳምጠው ተሰማን በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዷል።
46 min
22 February 2026
እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው?
ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ሆነዋል።
45 min
15 February 2026
እንወያይ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን?
47 min
15 February 2026
እንወያይ፤የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን?
በ2010 ዓ/ም እንደገና የጀመረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ አድናቆት የተቸረው እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርን የሰላም ኖቬል እስከማሸለም የደረሰ ነበር።ይሁንና የሀገራቱ ሰላማዊ ግንኙነት የዘለቀው ለጥቂት ዓመታት ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አለመግባቱ እየተካረረ መጥቷል።
47 min
08 February 2026
የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔ
41 min
08 February 2026
የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔ
የፌደራል ኃይሎች ከአወዛጋቢዎቹ ከአላማጣ እና ኮረም እንዲሁም ከሌሎች አጎራባች ከተሞች መውጣታቸው ከተሰማ በኋላ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ከከተሞቹ መሸሽ መጀመራቸው ሌላው ስጋቱ እንዲጨምር ያደረገ ክስተት ነበር። በትግራይ የድሮን ጥቃቶች በሁለት አካባቢዎች ተፈጸሙ የመባሉ ዜና በሀገር ውስጥም በውጭም ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።
41 min
01 February 2026
ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር?
44 min
01 February 2026
ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር?
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤iኢትዮጵያ እና ግብፅጽን ዳግም ወደ ድርድር ለማምጣት ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ደጋግመው ገልፀዋል.።ያም ሆኖ ትራምፕ በተለያዩ ጊዜዎች የሚሰጧቸው ወደ ግብፅ ያዘነበሉ አስተያየቶች የገለልተኝነት እና የፍትሃዊነት ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም።
44 min
25 January 2026
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ?
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
40 min
25 January 2026
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ?
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
40 min