እንዶድ፡ የትውውቅ ዝግጅት ፩ | እንዶድ እንደምን ያለ ነው?

እንዶድ፡ የትውውቅ ዝግጅት ፩ | እንዶድ እንደምን ያለ ነው?

Shega Creatives P.L.C
02:00:07
Link

About this episode

እንዶድ የራድዮ መሰናዶ በFM Addis 97.1 ዘወትር ረቡዕ ምሽት ከ 2:00 -4:00 ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ2:00 -4:00 ወደተወደዳችሁ አድማጮቹ ሊደርስ ዝግጅቱን አጠናቋል! 'አይነኬ' የሚመስሉ የግል እና የማህበረሰባዊ ስነ-ልቦናችን ርዕሰ ጉዳዮች ይነሱበታል!

"ከ'ኛው ለ'ኛው!" በግል እና በማህበራዊ ሕይወታችን ለገጠሙን ችግሮች መፍትሄ እናስሳለን፤ ባስ ብሎም መቆምያ መቀመጫ ላሳጡን ሕመሞቻችን መድህን እንቀያይጣለን!

14 ነን! ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰባስበናል! አንድ የጋራ ጉዳይ አለን! የታመመች ዓለም፣ አህጉር፣ አገር! ግብዞችም አይደለንም፤ እንፈጽማለን ብለን ማንንም አልሸነግልንም፤ ግን እናዋጣለን!!! አዎን ' ለተሻለ ነገ እናዋጣለን!' ብለን ተነስተናል!

አግዙን፤ ትውልድ እናግዝ! አግዙን፤ ዛሬን ሽረን ነገን እናልማ! አግዙን፤ ያጣናቸውን ትተን ያሉንን ላለማጣት አብረን እንቆም ዘንድ አብረን (አ'ብ'ረን) ዘብ እንሁን!

በትልቋ ዓለማችን ውስጥ 'ኢምንቶች' መሆናችንን ላ'ፍታ አንዘነጋም! ሆኖም ብዙ ኢምንቶች ከሁሉም ገዛፋ ጀርባ አሉና በዝታችኹ አግዝፉን። ከቶውኑ ባንጠቅማችሁ እንኳ' ሌላ አናጎድልም፣ ቢቀር ቢቀር ሲጎድልም ዝም ብለን የማናይ ነንና አግዙን!