zeno
Home
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Log in
Sign up
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
12
22 October 2025
የዶላር ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ሣምንት ብቻ ከአምስት ብር በላይ ጨመረ
ባለፈው አንድ ሣምንት ንግድ ባንክ ዶላር የሚገዛበት እና የሚሸጥበት ተመን አምስት ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ከፍ ብሏል። የብሔራዊ ባንክ አመልካች ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን በአንጻሩ 150 ብር ከ90 ሳንቲም ደርሷል። ብር በውጭ ምንዛሪ ገበያው መዳከሙን ሲቀጥል ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ለመውሰድ በድጋሚ ዝቷል።
22 October 2025
የምጣኔ ሀብት ምሁር ተመራማሪና ካህን ዶክተር ያብባል ሙሉዓለም ዋሴ
ዶክተር ያብባል የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ብቻ አይደሉም፤ካህንም ጭምር እንጂ። በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር ከተማ ተወልደው ያደጉትና የ1ኛና የ2ተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን የተከታተሉት ያብባል 2ተኛ ደረጃን እስኪጨርሱ ድረስ ትኩረታቸው በቀለም ትምሕርት ላይ ብቻ ነበር። ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ ግን የቤተ ክህነት ትምሕርትም ቀልባቸውን ሳበ።
22 October 2025
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋት
ትግራይ ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታውቋል።CPJ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
22 October 2025
ኒኮላ ሳርኮዚ ፤ በፈረንሳይ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት
በተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ሳርኮዚ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ ሆነው በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ተናግረዋል። የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።
22 October 2025
የመንገድ ብልሽት በመተከል ዞን
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ፣ ቡሌን እና ድባጢ የተባሉ ወረዳዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ በመበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለት ሳምንት ያህል መስተጓጉሉ ተገለጸ።
22 October 2025
የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች
ከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔው የሚጎዳ ነው ተብሏል።
22 October 2025
የደወሌው የባቡር አደጋ ያስከተለው ጉዳት
ባሳለፍነው ሰኞ ሌሊት በድሬደዋ ደወሌ የባቡር መጓጓዣ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 15 መሆኑን የድሬደዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት አስታወቀ።
21 September 2025
የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»
ህወሐት በአለፈው እሁድ ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።
24 August 2025
እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎች
ውይይቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ይረዳል በሚል በመስጠት ላይ ስለሚገኘው የክረምት ልዩ ስልጣና ምንነት እና ስለገጠሙት ፈተናዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሊጀምር የአንድ ወር እድሜ ያህል እንደመቅረቱ ከትምህርት ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል።
17 August 2025
ዝምታ ያጠላበት ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ
ሁለት ዓመት በዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በርካታ አዋቂና አዳጊ ሴቶች ለወሲብ ጥቃት መዳረጋቸውን የሀገር ውስጥም ሆኑ ዓለም አቀፍ የመብት ተቆርቋሪ ተቋማት በይፋ ገልፀውታል።