እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከጨለማው አለም ወደ ብርሃኑ መንግስት ካመጣን በኃላ ብቻችንን የተወንና በራሳችን እንድንቆም የለቀቀን አይደለም:: ነገር ግን ዘወትር በእጁ የተያዝንና የተጠበቅን ነን እንጂ::
የምናልፍበትና ያለንበት ሁኔታ የሚያስፈራ ደግሞም ብቻችንን የሆንን የተተውንም መስሎ ቢታየንም እንኳ በዚህም ውስጥ አጁ ይዛናለች:: ትመራናለችም:: የጠራን ጌታ እርሱ የታመነ ነው::
- ጌታ ይረዳኛልና አለፈራም ተብሎ እእደተፃፈ በእምነት ፀንተን እንቁም::