በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንደርሳለን፣ ጌታን እንደግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበልና በሐጢያታችን ስንናዘዝ ጌታ ይቅር ይለንና ልጆቹ ያደርገናል፣ ዳግመኛ በእውነት ቃል ከማይጠፋው ዘር እንወለዳለን፣ ጌታን ካወቅን በኋላ ንስሐ ያልገባንበት ሐጢያት ካለ የእግዚአብሔር ለሆነው ነገር ጠንካሮች እንዳንሆንና በጉስቁልና እንድንኖር ያደርገናል፣ እግዚአብሔር ከሐጢያት ጋር ሕብረት ስለሌለው ከጌታ ጋር ህብረት እንዳይኖረንም ያደርጋል፣ ስለዚህ እራሳችንን ሁልጊዜ አየመረመርን በንስሐ የእግዚአብሔርን ፊት ልንፈልግ ይገባናል፣