Endod Radio
Endod Radio

እንዶድ፡ንጽህና ነው!

የቀን ተቀን የኑሮ ውጣውረድ ያቆሸሸው በጥቂት ጥረት እና በውሃ ሙልጭ ብሎ የሚለቅበት፤ ቀድሞ ወደነበሩበት የሰውነት ክብር የሚመልስ ንጽህና! ለተጎናጸፈው ብቻ ሳይሆን ለሚያየው ሁሉ መልካም ስሜትን የሚያጭር ፀዓዳ!

እንዶድ ፡ መድኃኒት ነው!

ውስጥ ውስጡን የሚገዘግዝ፣ ሰላም የሚነሳን ብሽታ መንግሎ የሚጥል መድህን፤ ታመው ከማቀቁበት አልጋ አፈፍ ብለው የሚነሱበት ተፈጥሮአዊ ቅመም ነው፤ እጅግ የበረከተውን ወዳጅ ነጣቂ በሽታ “በቃህ” ሲል ያስቆመ የአልቃሽ አይኖች እረፍት ነው።

እንዶድ ፡ ተፈጥሮን የመመርመር ጽናት ማሳያ ነው!

የሩብ ምዕተ ዓመት ጽናት ውጤት፤ ተፈጥሮን መርምሮ ለራስ እና ለሌሎች ውጤቱን የማቋደስ ጽናት ነው። ጥልቁን ተፈጥሮ በተለይም የሰው ልጅን ያለመታከት መርምሮ ለግል እና ለወል ህይወቱ እፎይታን የመቸር ምሳሌ ነው።

እንዶድ ፡ ኃላፊነት ነው!

የሌላውን ስቃይ እንደራስ ቆጥሮ ለማስታገስ የመታተር ምሳሌ፤ የወገንን እምባ ለማበስ ዕድሜን የመገበር ያህል ከባድ ኃላፊነት፤ እንቅፋት ቢበዛም፣ ቀን ቀንን እየወለደ ከወጠኑት መድረስ ቅዠት ቢመስልም ሁሉን ችለው ዳር የሚደርሱበትን ጽናት የሚወልድ ኃላፊነት ነው።

Follow us

Let’s follow our station on social media!